የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብጹዓን አባቶች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ብጹዓን አባቶች ሞጆ በሚገኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሱባኤ ማዕከል ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል።
ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለአራት ቀናት በማዕከሉ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት መደበኛ ጉባኤ ሐዋርያዊ መልዕክት በማስተላለፍ ተጠናቅቋል፡፡
በጉባኤው ላይ ከቤተ ክርስቲያኗ ተልዕኮና መዋቅራዊ ጉዳዮች ባሻገር በሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የተለያዩ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።
በጉባኤው የተሳተፉ ብፁዓን ጳጳሳት ለሀገራችን ከምንግዜውም በበለጠ አንድ በመሆን ስለ ሰላም ድምጻችን እንዲሰማ እንሻለን ብለዋል።
ብጹዓን አባቶች ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ በየአመቱ የሚያድርጉትን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ያከናወኑ ሲሆን፥ ምድርን መንከባከብ የሁሉም ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡