Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በአሶሳ ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዛሬው ዕለት በአሶሳ ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ከንቲባዋ በከተማዋ በሚገኘው ሀለዋ የአግሮ ኢንዱስትሪ መንደር የሌማት ትሩፋት ስራዎችን የጎበኙ ሲሆን፥ የዶሮ፣ የእንቁላልና የወተት ተዋፅኦ በቀላል መንገድ በማልማትና የአካባቢ ሀብትን በመጠቀም እንዴት ምርታማነትን መጨመር እንደሚቻል ተመልክተናል ብለዋል፡፡
አዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ከክልሎች ጋር የምርት አቅርቦት ትስስር በመፍጠር ምርትን ወደ ከተማዋ ለማስገባት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቆይታቸው በኮሪደር ልማት ስራዎች የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.