Fana: At a Speed of Life!

የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በ82 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሙሃማዱ ቡሃሪ ባደረባቸው ሕመም ሕክምና ሲከታተሉ በነበሩበት ለንደን ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የናይጄሪያ ቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በፈረንጆቹ ከ1983 እስከ 1985 በሀገሪቱ በወታደራዊ አመራርነት ያገለገሉ ሲሆን ÷ ከ2015 እስከ 2023 ደግሞ በፕሬዚዳንትነት ተመርጠው አገልግለዋል።

የሙሃማዱ ቡሃሪ የቀብር ሥነ ሥርዓት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንደሚከናወንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.