Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስአበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ላይ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከተወያየ በኋላ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

በመቅደስ አስፋው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.