የከተማ አስተዳደሩ ለገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች እውቅና ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች የእውቅና እና ምስጋና መርሐ ግብር አከናውኗል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፥ በከተማ አስተዳደሩ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት 233 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡
በዚህም የከተማዋ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የከተማችንን የልማት ስራዎች በላቀ ደረጃ እንድንፈፅም አስችለውናል ብለዋል፡፡