በክልሉ የሀብት ብክነት እንዳይኖር በትኩረት መስራት ይገባል – አቶ ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የሀብት ብክነት እንዳይኖር በትኩረት መስራት ይገባል አሉ።
የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ኦዲት ሪፖርት ቀርቧል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት በክልሉ የሀብት ብክነት እንዳይኖር በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበው÷ የሕዝቡ የልማት ጥያቄ እንዲመለስ የተመደበው በጀት በሥራ ላይ መዋል አለመዋሉን የክልሉ መንግስት ክትትል ያደርጋል ብለዋል።
የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ያለውን ገንዘብ ሕግን በተከተለ መንገድ እንዲጠቀሙና በአግባቡ በሥራ ላይ እንዲያውሉም አሳስበዋል።
ምክር ቤቱ በቀረበው የኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በታመነ አረጋ