የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ክልል 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የቀረቡ ሹመቶችን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ተጠናቅቋል።
በዚህም መሠረት አቶ ቢኒያም ሰለሞን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የፍርድ ቤት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ገነነ ሹኔ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንትና የአስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
እንዲሁም ዳዊት ዳንግሶ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ፤ አቶ ፍቅረየሱስ አሸናፊ ደግሞ የመሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
ተሿሚዎቹ ተገልጋዩ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ኃላፊነታቸውን በማሰብና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፈተሸ እንዲፈቱ በማሰብ የተመረጡ መሆናቸውን አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ባለፈው በጀት ዓመት ጥሩ አፈፃፀም ላሳዩት የክልሉ የሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የጤና ቢሮና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክር ቤቱ ዕዉቅና ሰጥቷል።
በጥቅል ውጤት እንዲመጣ ላስቻሉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የምክር ቤቱ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።
በታመነ አረጋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡