Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በጁገል ቅርስ ያለማው መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ያለማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሀረሪ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ምቹ ለማድረግ መንገዶችን ከመገንባት ባለፈ የአካባቢውን ንፅህና በመጠበቅ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

የጁገል ቅርስ ለነዋሪዎች ብሎም ለጎብኚዎች ምቹ እንዲሆን በርካታ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰው፥ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የኮሪደር ልማት ስራ በማከናወን አሻራውን አኑሯል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በዕውቀትና ክህሎት ከማነፅ ባለፈ የኢትዮጵያውያን ኩራትና የዓለም ሀብት የሆነውን የጁገል ቅርስ ሀብት እንዲያመነጭ ለማስቻል በሚደረገው ርብርብ በመሳተፍ ላከናወነው ስራና በቅርስ ጥበቃ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣቱ አመስግነዋል።

ዩኒቨርሲቲው ያከናወነው ተግባር ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በቀጣይም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ መሰል ማኅበራዊ ዘርፎች ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ100 ሜትር በላይ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መልሶ ማልማቱን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.