Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጤናው ዘርፍ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጤናው ዘርፍ ከ1 ሚሊየን 200 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ ታመነ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ10 የተለያዩ የህክምና ዘርፎች ለሕብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣል።

በዚህም የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የጡት ካንሰር፣ የማህፀን ጫፍ ካንሰርና የቲቪ ምርመራና ህክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

እንዲሁም የዓይንና የጆሮ ምርመራና ህክምና፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ምርመራ፣ የሥርዓተ ምግብ ልየታ እና ደም መሰብሰብ ተግባራት እንደሚከናወኑ አብራርተዋል።

በተጨማሪም የወባ እና የሌሎች ለወረርሽኝ ስጋት የሆኑ በሽታዎች ስርጭትን መቆጣጠር እና መከላከል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በክልሉ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በጤናው ዘርፍ 1 ሚሊየን 226 ሺህ 950 የሕብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አመልክተዋል።

በጤናው ዘርፍ በሚሰጡ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከመንግስት እና ሕዝብ ሊወጣ የሚችል ከ40 ሚሊየን ብር በላይ  ወጪ ለማዳን እንደሚሰራ አቶ ምትኩ ጠቁመዋል።

በመርሐ ግብሩ  የተለያዩ የጤና ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.