Fana: At a Speed of Life!

የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚው ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እየተከተለችው ያለው የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫ በቱሪዝም ዘርፉ ለሰው ሀብት ልማትና መዳረሻዎችን በማስፋት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል አሉ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዲግሪና በደረጃ ለ57ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ሚኒስትሯ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንዳሉት፥ በቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት፣ በሰው ኃይል ግንባታና የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችን በማስፋት አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ተመራቂዎች በተማሩባቸው የሙያ ዘርፎች ለሀገራቸው ዕድገትና ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ነጋሽ በበኩላቸው፥ ኢንስቲትዩቱ ስልጠናዎቹን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ያሟሉ ለማድረግ በርካታ የምርምርና ጥናት ስራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.