በባንግላዲሽ ጄት ተከስክሶ ህጻናትን ጨምሮ የ27 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባንግላዲሽ አየር ኃይል ጄት በትምህርት ቤት ላይ ተከስክሶ 25 ህጻናትን ጨምሮ የ27 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በዋና ከተማዋ ዳካ በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ 170 ሰዎች ጉዳት እንደደረሳበቸው የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
የሀገሪቱ ጦር እንዳስታወቀው የጦር ጄቱ የተከሰከሰው በልምምድ ላይ በነበረበት ወቅት ሲሆን፥ የቴክኒክ እክል እንደገጠመው ነው የተገለጸው፡፡
ጄቱ በትምህርት ቤቱ ህንጻ ላይ ሲወድቅ በእሳት ተያይዞ እንደነበር የዐይን እማኞችን ጠቅሶ የዘገበው ሮይተርስ ነው፡፡