አየር መንገዱ በ150 ሚሊየን ዶላር ያስገነባቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ150 ሚሊየን ዶላር ያስገነባቸውን ፕሮጀክቶች አስመረቀ፡፡
አየር መንገዱ ያስመረቃቸው ፕሮጀክቶች የአውሮፕላን ክፍሎች መጠገኛ፣ የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ከሰው ንከኪ ነፃ የሆነ መጋዘን ነው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ እና የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፤ ፕሮጀክቶቹ የአየር መንገዱን ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋሉ ብለዋል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፤ መሰረተ ልማቶቹ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂዎች አካትተዋል ነው ያሉት።
የተመረቁት መሰረተ ልማቶች የአየር መንገዱን ፈጣን እድገት ለመደገፍና ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ እንደሚያስችሉም ገልጸዋል።
በኤፍሬም ምትኩ