Fana: At a Speed of Life!

በሌማት ትሩፋት 13 ቢሊየን ሊትር ወተት ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስቴር በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር 13 ቢሊየን ሊትር ወተት ተመርቷል አለ፡፡

በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የሌማት ትሩፋት በምግብ እራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ በተለይም በወተት ምርት ላይ በተከናወነ ሥራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጨባጨ ውጤት መመዝገቡን ነው ያብራሩት፡፡

በዚህም የወተት ላም ዝርያን ለማሻሻል መሰራቱን ጠቁመው÷ በበጀት ዓመቱ 5 ነጥብ 9 ሚሊየን የወተት ላሞችና ጊደሮችን የማዳቀል ሥራ ተከናውኗል ብለዋል፡፡

የተቀናበረ የመኖ አቅርቦትን በማሳለጥ የወተት ምርትን ለማሳደግ በትኩረት መሰራቱንም ሚኒስትር ዴዔታው ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 12 ቢሊየን ሊትር ወተት ለማምረት ታቅዶ 13 ቢሊየን ሊትር ወተት ተመርቷል ነው ያሉት፡፡

የተገኘው ምርት የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ከመጀመሩ በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የ6 ቢሊየን ሊትር ብልጫ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.