Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ቁርጠኛ ናት – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ቁርጠኛ ናት አሉ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፡፡

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በዓለም ንግድ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ጄኔቫ ገብተዋል፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎንም ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ቁርጠኛ ናት፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ በኩል እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶችን እና ለ6ኛው የሥራ ቡድን ስብሰባ ያለውን ዝግጁነት አብራርተዋል።

ኒኮዚ አዌላ(ዶ/ር) ጋር በበኩላቸው ÷ ለረጅም ጊዜ ሲንከባል የነበረውን የኢትዮጵያን የአባልነት ድርድር ለማጠናቀቅ በሁሉም ደረጃ ባሉ የመንግስት አካላት ያለው ቁርጠኝነት አስተማማኝ ነው ብለዋል፡

ድርድሩን በታቀደለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ይህንኑ ፍጥነትና ትጋት ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የአባልነት ድርድር 6ኛው ዙር የሥራ ቡድን ስብሰባ በመስከረም ወር መጨረሻ ላይ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ መደረሱንም የገንዘብ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

አስቀድሞ በታቀደው መሰረት የድርድር ሒደቱን በፈረንጆቹ መጋቢት 2026 በካሜሩን በሚካሄደው የድርጅቱ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ለማጠናቀቅ ያለማቋረጥ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.