Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የተለያዩ የምስጋና ስጦታዎችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ የምስጋና ስጦታዎችን ለደንበኞቹ አበርክቷል።

በዚህ መሰረትም ለ3 ቀናት የሚያገለግል 1 ጂቢ የኢንተርኔት፣ በየቀኑ የ5 ደቂቃ የድምጽ እና በየቀኑ 8 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ስጦታን ለደንበኞቹ አበርክቷል፡፡

እንዲሁም የ10 ደቂቃ ዓለም አቀፍ ጥሪ የምስጋና ስጦታን ለደንበኞቹ ማበርከቱ ነው የተመላከተው፡፡

ስጦታዎቹን ከዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 12 ሰዓት ድረስ መጠቀም እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተከትሎ ነው ለደንበኞቹ የምስጋና ስጦታ ያበረከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.