Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2018 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል።

የክልሉ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ የኮሙኒኬሽንና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቶሎሳ አጃማ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተያዘው ዕቅድ ተሳክቷል።

በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ቋሚ የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን ገልጸው፤ የሥራ ዕድል ለሚፈጠርላቸው ዜጎች 98 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚቀርብ ጠቁመዋል።

እንዲሁም 15 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ብድር እንደሚቀርብ እና ለ3 ሚሊየን ዜጎች የኢንተርፕርነርሽፕ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጹት።

በተጨማሪም ለ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች አጫጭር ስልጠናዎች እንደሚሰጥ እና 185 ሺህ ነባርና 143 ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ለማስገባት ዕቅድ መያዙን አስረድተዋል።

በበጀት ዓመቱ የስራ ዕድል ፈጠራው ክህሎት መር እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በአድማሱ አራጋው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.