Fana: At a Speed of Life!

ኢፋድ አካታችና ዘላቂ የግብርና ልማትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (ኢፋድ) ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሪዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የኢፋድ ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሪዮ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ ብለዋል።

ተቋሙ የገጠሩን ማኅበረሰብ በማብቃት አካታች እና ዘላቂ የግብርና ልማት ለማሳደግ አይነተኛ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡

ለፈተና የማይበገር አኗኗርን ለመገንባት ከተቋሙ ጋር ላለን ጠንካራ ትብብር እና የጋራ ተልዕኮ ከፍ ያለ ዋጋ እንሰጣለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.