Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ ጀንበር 60 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በመጪው ሐሙስ በአንድ ጀንበር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን 60 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አንደኛ ሽናሌ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ በዕለቱ ከሚተከሉት ችግኞች ውስጥ 23 ሚሊየን የሚሆነው ጅኦግራፊያዊ መገኛው ይመላከታል፡፡

በክልሉ በዚህ ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ380 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ 42 ሚሊየን የሚሆነው የፍራፍሬ ችግኝ መሆኑን ገልጸው፥ እስካሁን በበልግ እና በክረምት 222 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል ነው ያሉት፡፡

በክልሉ የሚተከሉት ፍራፍሬ፣ የመኖ፣ የደን፣ የቀርከሃ እና ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የሚሆኑ ችግኞች መሆናቸውንም ነው ምክትል ኃላፊው የተናገሩት፡፡

በክልሉ ለሚከናወነው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የጉድጓድ፣ የችግኝ፣ የተከላ ቦታዎችን ጂኦግራፊያዊ ቦታ የማመላከትና መሰል ዝግጅቶች ተደርገዋል ብለዋል፡፡

የሚተከሉት ችግኞች የታለመላቸውን ዓላማ እንዲያሳኩ ማህበረሰቡ በዕለቱ የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ አቶ አንደኛ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በመሳፍንት እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.