Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን በግብርናው ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና የጣሊያን የግብርና ሚኒስትር ፍራንሲስኮ ሎሎብሪጊዳ ፈርመዋል።

ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት ከዚህ በፊት የነበራቸውን ትብብር የሚያጠናክርና በተለይም የቡና ሰንሰለቶችን የማዘመን ስራ ላይ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተነስቷል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ስምምነቱ ጣሊያን ግብርናን በማዘመን በአውሮፓ ያላትን ቀዳሚ አቅም ለመጋራት ያስችላል፡፡

የጣሊያን አቻቸው ፍራንሲስኮ ሎሎብሪጊዳ በበኩላቸው፥ በግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ መስራት የሚያስችሉ አማራጮች ላይ ስምምነት መፈፀሙን አንስተዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.