Fana: At a Speed of Life!

110 ሺህ ነዋሪዎችን ከጎርፍ አደጋ መታደግ የሚያስችል የጎርፍ መከላከል ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ገቢ ረሱ ዞን ዱለቻ ወረዳ 110 ሺህ ነዋሪዎችን ከጎርፍ አደጋ መታደግ የሚያስችል የጎርፍ መከላከል ስራ እየተሰራ ነው አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡

ሚኒስትሩ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የጎርፍ መከላከል ስራዎችን በተመለከቱበት ወቅት እንዳሉት፥ በዚህ ክረምት በክልሉ ዱለቻ፣ ገዋኔ እና አይሳኢታ ወረዳዎች በ383 ሚሊዮን ብር በጀት 96 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻዎችን የመጥረግ ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

በዚህም እስከ ዛሬ በየዓመቱ የጎርፍ ውሃ እየተኛበት ጥቅም ላይ ይውል ያልነበረ 32 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

የአዋሽ ተፋሰስን ጨምሮ ሌሎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ በጥናት የተደገፉ ዘላቂ የጎርፍ መከላከል ስራዎችን ለመስራት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል።

የወረዳዋ ነዋሪዎች በአካባቢው በከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የጎርፍ አደጋ ስጋት እንደነበር ገልጸው፥ የንብረትና የህይወት ጉዳቶችን ሲያደርስ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ በወረዳው እየተከናወነ ባለው የጎርፍ መከላከል ስራ ከጎርፍ ስጋት ነጻ ሆነው በሙሉ አቅማቸው ወደ እርሻ ስራ መግባታቸውን ነው የገለጹት፡፡

በትዝታ ደሳለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.