የሆስፒታሉ አረንጓዴ ምድረ ግቢ የሚመችና ፅዱ የሥራ ከባቢ ፈጥሯል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታል አረንጓዴ ምድረ ግቢ ለህክምና አገልግሎት የሚመችና ፅዱ የሥራ ከባቢ ፈጥሯል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ኮምፕሬሄንሲቭ ሆስፒታልን የለውጥ ስራዎች ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ሆስፒታሉ ከለውጡ በፊት ታካሚዎችን ለእንግልት ሲዳርግ የቆየውን የአገልግሎት አሰጣጥ በመሰረታዊነት የቀየረ ስራዎችን አሁን እውን አድርጓል ብለዋል።
በተለይ ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት የሚያዘምኑ የጤና መሠረተ ልማቶችን በማሟላት ሰፊ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶችና ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁስን በማሟላት ለተጠቃሚው የሕብረተሰብ ክፍል ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ የአገልግሎት ማሻሻያና የማስፋፊያ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቁመዋል።
የሆስፒታሉ አረንጓዴ ምድረ ግቢ ለህክምና አገልግሎት የሚመችና ፅዱ የሥራ ከባቢ እንዲፈጠር አድርጓልም ነው ያሉት።
በሌላ በኩል በጅግጅጋ ከተማ ሁሉን አቀፍ እንዲሁም ዘመኑን የዋጀ የተቋም ግንባታ እያከናወኑ የሚገኙትን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤትን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
ተቋማቱ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂና በቢሮ እድሳት አስደናቂ ለውጥ ላይ እንደሚገኙ ተመልክተናልም ነው ያሉት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!