Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በየመን በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡

በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ለሕልፈት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

መንግሥት ዜጎች በተለያዩ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁም አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.