የኢትዮጵያ አየር መንገድ 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ።
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ÷ አየር መንገዱ ዘመኑን የዋጀ አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ነው።
በዓመቱ 6 ዓለም አቀፍ ጣቢያዎች መክፈት የቻለው አየር መንገዱ፥ 13 የተለያዩ አውሮፕላኖች ወደ ስራ አስገብቷል ነው ያሉት።
በ2017 በጀት ዓመት 19 ሚሊየን መንገደኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ መጓጓዛቸውን ነው የተናገሩት።
ከመንገደኞችና ዕቃ ጭነት አገልግሎትም 7 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም አመልክተዋል።
በዓመቱ በዘርፉ በርካታ አሉታዊ ክስተቶች መከሰታቸውን አንስተው በተለይም በተለያዩ ሀገራት በተፈጠረው ጦርነት በረራዎች ተስተጓጉለዋል ብለዋል።
አሁን ላይ የአየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎች 21 መሆናቸውን ጠቁመው፥ በቅርቡ የሚጠናቀቁ የ5 መዳረሻዎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አየር መንገዱ በጭነት አገልግሎት 785 ሺህ 323 ቶን በላይ ካርጎ እንዳጓጓዘ ተናግረዋል።
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!