የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ያነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች፡- On Aug 5, 2025 175 የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የዓለምን 7 በመቶ ህዝብ ይወክላሉ ኢፍትሃዊ የሆነው የዓለም የንግድ ስርዓት እነዚህን ሀገራት ያገለለ ነው ሀገራቱ ለከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ ተዳርገዋል፤ የንግድ ተሳትፏቸው ተገድቧል ተገማች ላልሆነው የዓለም የሸቀጦች ዋጋ ተጋላጭ ሆነዋል በውስን የኢኮኖሚ መሰረት ላይ እንዲቆዩ ተገድደዋል የሀገራቱ ስኬት ለአጀንዳ 2030 መሳካት ወሳኝ ነው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሊታረሙ ይገባል በማለት ያነሷቸው ሀሳቦች፡- የባህር በር አልባ መሆን የሀገራትን እጣፈንታ ሊወስን አይገባም ሀገራቱ እየተጋፈጡት ያለውን ኢፍትሃዊ የንግድ ስርዓት በአፋጣኝ ማሻሻል ያሻል በሀገራቱ የመልማት እድሎች ላይ የተጋረጡትን ገደቦች ማንሳት ያስፈልጋል በቀጣይ አስር ዓመታት መስራት ይጠበቅብናል ያሏቸው 4 መሰረታዊ ጉዳዮች፥ መዋቅራዊ ለውጥና ብዙሃንን ያማከለ ኢኮኖሚን ገቢራዊ ማድረግ ንግድንና ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም ጥረቶችን ማጠናከር ለሀገራቱ የፋይናንስ ድጋፍና አጋርነትን ማጠናከር የተባበሩት መንግስታት የባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄና ጥረት በመደገፍ ከሀገራቱ ጎን ይቆማል በኃይለማርያም ተገኝ 175 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint