በክልሉ ከ2 ሺህ 600 በላይ የትምህርት ቤት አመራሮችና መምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 254 የትምህርት ቤት አመራሮችና 2 ሺህ 359 መምህራን የክረምት ልዩ አቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ነው።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ልማት ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ መምህራንና አመራሮቹ በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ስልጠናው መምህራን በሚያስተምሯቸው የትምህርት ዓይነቶች የሚሰጥ መሆኑን አንስተው÷ ከመምህራን ማስተማር ጋር ቀጥታ የተገናኘ በማስተማር ስነ ዘዴ ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ቴክኖሎጂን ለመማር ማስተማር ስራ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቅሰው÷ መምህራን ብቁ ሆነው ዕውቀታቸውን ለተማሪዎቻቸው ማስተላለፍ የሚችሉበትን ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።
በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች የተዘጋጀ ሞጁሎችን በመጠቀም የትምህርት አመራሮች በመማር ማስተማር ስራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ የሚያስችል ስልጠናው እንደሚሰጣቸውም አመልክተዋል።
ስልጠናው የትምህርት ጥራት ችግርን ለመፍታት በቀጥታ ከተማሪዎች ጋር የሚገናኙ መምህራን እና አመራሮች ከሚያስተምሩት የትምህርት ይዘት ጋር በተናበበ መልኩ የሚሰጥ በመሆኑ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው ብለዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!