Fana: At a Speed of Life!

ሞስኮ የገቡት የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ዙሪያ ለመምከር ሞስኮ ገብተዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛው በሞስኮ ቩንኮቮ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሩሲያ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኪሪል ዲሚትሪቭ አቀባበል አደርገውላቸዋል፡፡

ዊትኮፍ በቆይታቸው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ለማምጣት ያለመ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚቲሪ ፔስኮቭ የዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ሊወያዩ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸውን የአር ቲ ዘገባ አመላክቷል፡፡

በኔቶ የአሜሪካ አምባሳደር ማቲው ዊትከር የልዩ መልዕክተኛው ጉብኝት የሩሲያ እና ዩክሬንን ጦርነት ሊያስቆም እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

በቅርቡ አሜሪካ እና ሩሲያ የዩክሬንን ጦርነት በተመለከተ ውጥረት ውስጥ መግባታቸውና ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እጥላለሁ ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሩሲያና ዩክሬን ወደ ሰላም ስምምነት እንዲመጡ ግፊት እያደረጉ ሲሆን÷ ሁለቱ ሀገራት በሦስት ዙር በኢስታንቡል ባደረጉትና ያለስምምነት በተጠናቀቀው ድርድር የፕሬዚዳንቱ ሚና ከፍተኛ እንደነበረም ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.