Fana: At a Speed of Life!

ቪያሪያል የቶማስ ፓርቴን ዝውውር አጠናቀቀ

‎አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቪያሪያል የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጫዋች የነበረው የቶማስ ፓርቴን ዝውውር አጠናቅቋል።

ቪያሪያል የ32 ዓመቱን የቀድሞ የመድፈኞች ተጫዋች ቶማስ ፓርቴ በነጻ ዝውውር የግሉ ማድረግ ችሏል።

ጋናዊው ተጫዋች በነጻ ዝውውር የስፔኑን ክለብ የተቀላቀለ ሲሆን÷ ለሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት መፈራረሙን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

በፈረንጆቹ 2020/21 የውድድር ዓመት ከአትሌቲኮ ማድሪድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ፓርቴ 167 ጨዋታዎችን ለመድፈኞቹ አድርጓል፡፡

የስፔኑ ክለብ ቪያሪያል የቶማስ ፓርቴ ይፋዊ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.