አህጉራዊ የቡና ንግድ ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ቡና ንግድ ዓውደ ርዕይ ከጥር 27 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡
ለ22ኛ ጊዜ የሚካሄደው ዐውደ ርዕዩ የአፍሪካ ቡና ኢንዱስትሪ እድገትን ለማጠናከር እና በዘርፉ ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስርን መፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በ2024 መርሐ ግብሩን ያስተናገደች ሲሆን፥ መንግስት አሁን ላይ ለዘርፉ የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በድጋሚ ለማስተናገድ እንድትመረጥ ማስቻሉ ተጠቅሷል፡፡
መድረኩ በአፍሪካ ልዩ ጣዕም ያላቸው ቡናዎችን በማስተዋወቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነታቸውን ለማሳደግ እንደሚያግዝም ተጠቁሟል፡፡
በመድረኩ ከተለያዩ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የቡና አምራቾችና ላኪዎችን ጨምሮ ከ2 ሺህ በላይ የዘርፉ ተዋንያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
በመሳፍንት ብርሌ