ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ከመንገዷ ለማስቀረት ያቀዷቸው ስልቶች…
የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት ታሪካዊ ጠላቶችና የእነርሱ ተላላኪዎች ኢትዮጵያን ከመንገዷ ለማስቀረት የመጨረሻውን ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡
በዚህ የመጨረሻ ሙከራቸውም ስድስት ስልቶችን ለመጠቀም እንደተነሡ ነው ምክር ቤቱ የገመገመው፡፡
እነዚህ ስልቶችም፡-
👉ለግድያ የሚፈላለጉ ኃይሎችን በጥቅም ማስተሣሠር
👉ኢትዮጵያን በሑከት ውስጥ ማቆየት፤
👉 በመልካም አስተዳደር ችግር የተነሣ የሚፈጠሩ የሕዝብ ቅሬታዎችን ለዐመጽ መጠቀም፤
👉 ብሶት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን ማራገብ፤
👉ሚዲያዎችን የሑከት መቀስቀሻ መሣሪያ ማድረግ፤
👉በውጭ ምንዛሬ እና በሸቀጦች በኩል የኢኮኖሚ አሻጥርን መሥራት ናቸው።