የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት የታሪካዊ ጠላቶችን የመጨረሻ ሙከራ ለማምከን በቁርጠኝነት ለማከናወን ያስቀመጣቸው ሰባት ጉዳዮች፡-
የብልፅግና ፓርቲ ም/ቤት የታሪካዊ ጠላቶችን የመጨረሻ ሙከራ ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን በቁርጠኝነት ለማከናወን ያስቀመጣቸው ሰባት ጉዳዮች፡-
👉ግጭትን ሊያስቀሩ የሚችሉ ሰላማዊ አማራጮችን በሁሉም አቅጣጫ ለመሞከርና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለሚወስኑ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ፤
👉የሰላምን አማራጭ ባለመቀበል በሕዝብና በሀገር ንብረት ላይ ችግር ለመፍጠር በሚነሡ ኃይሎች ላይ በተጠናከረ መንገድ ሕግ ለማስከበር፤
👉በየደረጃው የሚነሡ የሕዝብ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በኢትዮጵያ ዐቅም ልክ በየደረጃው ለመመለስ፤
👉ተገቢውንና እውነተኛውን መረጃ ለሕዝብ በየጊዜው ለመስጠትና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማጋለጥ፤
👉በየተቋማቱ ተመድበው የዲሲፕሊን ጉድለት፣ሙስናና የአስተዳደር በደል የሚያደርሱ የሥራ መሪዎችንና አገልጋዮችን ለመታገል፤
👉በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ እንደዚሁም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመርናቸውን የልማት ሥራዎች የበለጠ ስኬታማ በማድረግ፤ የተጀመሩ ኢኒሼቲቮችን ለውጤት በማብቃት፤ የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ የከተማና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ፤
👉በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሁሉም መንገድ ለማስከበር፤