በክልሉ 89 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረዋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ 89 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረዋል አለ።
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ ላይ እየተወያየ ነው።
በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮው ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ እንዳሉት፤ በክልሉ የኢንዱስትሪዎች አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።
በ2017 በጀት ዓመት አዳዲስ ኢንዱስትሪን የመፍጠር ፣ በገበያ ትስስርና ኢንተርፕራይዞችን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በዘርፉ አበረታች ጅምር ሥራዎች መኖራቸው ገልጸው፤ በዚህም 89 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ተፈጥረው ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል።
በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን መርሐ ግብር የሚቋቋሙ 44 ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ በተያዘው በጀት ዓመት 180 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋም ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዷል ነው ያሉት።
በክልሉ የኢንዱስትሪዎች አቅም እያደገ በመሆኑ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ለውጭ ሀገር ገበያ ማቅረብ ጀምረዋል ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ በክልሉ ያለውን አቅም ለመጠቀም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
በፍሬው አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!