የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ያጠናክራል – ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 ፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ያጠናክራል አሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ፡፡
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
በመርሐ ግብሩ የአረንጓዴ አሻራ፣ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የቤት እድሳት እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር በመነቃነቅ ዓለምን ያስደመመ ተግባር እያከናወኑ ነው።
ሚኒስቴሩ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ችግር የሚያቃልሉ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብሮነትንና የእርስ በርስ ትስስርን ለማጠናከር እንደሚስችልም ነው የተናገሩት።
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡