ክሪስታል ፓላስ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሙዩኒቲ ሽልድ ዋንጫን አሸንፏል።
ከፍተኛ ፉክክር በታየበትና በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል።
ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባደረጉት ፍልሚያ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁ÷ የሊቨርፑልን ግቦች አዲስ ፈራሚዎቹ ሁጎ ኢኪቲኪ እና ጀረሚ ፍሪምፖንግ አስቆጥረዋል፡፡
የክሪስታል ፓላስን ሁለቱን ግቦች ማቴታ እና ኢስማኢል ሳር አስቆጥረዋል።
ጨዋታው በሁለት አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ያመሩት ቡድኖች ክሪስታል ፓላስ በመለያ ምት ሊቨርፑልን 3 ለ 2 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።