ከአርባምንጭ እስከ ወላይታ ስንጓዝ የአረንጓዴ ልማት ሥራችንን ውጤት ተመልክተናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከአርባምንጭ እስከ ወላይታ ስንጓዝ የአረንጓዴ ልማት ሥራችንን ውጤት ተመልክተናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ወላይታ ሶዶ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ጽኑ አቋማችን ምስክር ናት ብለዋል።
ከአርባምንጭ እስከ ወላይታ ስንጓዝ የአረንጓዴ ልማት ሥራችን ውጤት እንዲሁም አስደናቂ የፍራፍሬ እርሻ ልማት መስክ ተመልክተናል በማለት ገልጸዋል።
እነዚህ ጥረቶች የመልከዓ ምድሩን ልምላሜ ከመመለስ ባሻገር የአኗኗር ዘይቤንም የማሸጋገር ሥራዎች እንደሆኑ አመልክተዋል።
በጠንካራ የሥራ ባሕሉ እና ኅብረቱ የሚታወቀው የወላይታ ሕዝብ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ጠንካራ ሚና መወጣቱን ቀጥሏል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።