Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ1 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፈረንጆቹ ከሐምሌ 1 ቀን 2025 ጀምሮ ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈፅሜያለሁ አለ፡፡

ባንኩ ለፋና ዲጂታል በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ ባንኩ በየጊዜው ለደንበኞቹ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማቅረብ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞቻችን ማመልከቻዎችን ሁሉንም በማጽደቅ የ420 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች ፈቅዷል።

የዛሬው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከተፈቀደው ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ ባንኩ ለ1 ሺህ 140 ደንበኞች 541 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ተፈቅዷል።

ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሪ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ባንኩ በፈረንጆቹ ከሐምሌ 1 ቀን 2025 ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ 1 ነጥብ 34 ቢሊየን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ፈፅሟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞች ፍላጎት እና ከሀገር ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ጋር በማጣጣም ለውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመደበኛነት ምላሽ መስጠቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.