ከዝናብ ጠባቂነት ባህል የሚያሻግር የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ እየተከናወነ ነው – አብርሃም በላይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የግብርና ሥርዓት ከዝናብ ጠባቂነት ባህል የሚያሻግር የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ ነው አሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ።
ሀገር አቀፍ የመስኖ ፕሮጀክቶችን ጥራት የሚያስጠብቅ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ስታንዳርድ ዝግጅት ዓውደ ጥናት የማጠናቀቂያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ÷ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ካልተቻለ የሀገርን የተሟላ ሉዓላዊነት ማጎናጸፍ አይቻልም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በግብርና ዘርፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የመጣችበት መንገድ በዝናብ ጥገኝነት የተመሰረተና የመስኖ ፕሮጀክቶችም ወጥነት የጎደላቸው እንደነበሩ አስታውሰዋል።
በዚህም የኢትዮጵያን በዝናብ ላይ የተንጠለጠለ የግብርና ሥርዓት ለማስተካከል የተለያዩ የመስኖ ልማት አማራጭ የመፍትሔ ርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ከዚህ ቀደም ወጥ የሆነ የመስኖ ልማት ፍኖተ ካርታ አለመኖሩም በፕሮጀክት አፈፃጸም ላይ አሉታዊ ጫና ሲያሳድር እንደቆየ ነው ያብራሩት፡፡
የመንግስት ሃብት አዋጭ በሆነ ፕሮጀክት ላይ መዋል አለበት ያሉት ሚኒስትሩ ÷ ለዚህም ጥራታቸውን የጠበቁ የመስኖ ፕሮጀክቶች መገንባት የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጦ እተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሰነዱ በአዋጭነት ጥናት ላይ የተመሰረተ የመስኖ ፕሮጀክት የልማት ስራዎችን በታወቀ የአሰራር ሥርዓት ማከናወን የሚያስችል አካሄድ መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
በተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ፋራይ ዚሙድዚ በበኩላቸው ÷ የመስኖ ልማት የፕሮጀክቶች ጥራት ማስጠበቂያ ሰነድ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የመስኖ ልማት ጥራት ክፍተቶችን በመሙላት በዘመናዊ መመሪያና የቴክኒክ ደረጃዎች እንዲመራ የሚያስችል መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።
የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት የምግብና ግብርና ምርታማነት ዘላቂነትን በመደገፍ ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የሌለበትን ዓለም የመፍጠር ጽኑ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ የአባል ሀገራትን ዘላቂ የልማት ግብ ለማሳካት የግብርና ምርታማነትን የሚያሳልጥ ስትራቴጂካዊ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ነው ያስረዱት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!