የመጀመሪያው የቴምር ፌስቲቫል በኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በፌስቲቫሉ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ ከዘጠኝ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የግብርና ዘርፍ ሀላፊዎች፣ ተመራማሪዎች እና አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ አወል አርባ በፌስቲቫሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፌስቲቫሉ የቴምር ልማትን በቴክኖሎጂ እና ፈጠራ በመደገፍ ምርታማነት ለማሳደግ እጅግ ጠቃሚ ነው ብለዋል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዘላቂነት ያለው ግብርናን ለማስፋትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲህ አይነት ፌስቲቫሎች ከፍተኛ ሚና አላቸው ነው ያሉት።
እንደ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ እና ከፊል ኦሮሚያ ቴምርን የማልማት ምቹ ስነ-ምህዳር እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች ቴምር በማልማት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ሀገራዊ ጉዞ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
በፌስቲቫሉ ዘመናዊ የቴምር አመራረት ዘዴዎች ይዳሰሳል፣ የተለያዩ የቴምር ዝርያዎች ይተዋወቃሉ እንዲሁም ከበርካታ ሀገራት የመጡ የቴምር ልማት ተመራማሪዎች የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያ ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር በትብብር ያዘጋጀችው ይህ ፌስቲቫል ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ይቆያል።
በካሊፋ ከድር
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!