Fana: At a Speed of Life!

የካንሰር ሕክምና ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካንሰር ሕክምና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የጤና ሚኒስቴር።
በሚኒስቴሩ የካንሰር ሕክምና መርሐ ግብር አማካሪ ዶ/ር ኩኑዝ አብደላ እንዳሉት ÷ በኢትዮጵያ በየዓመቱ 80 ሺህ አዳዲስ የካንሰር ሕሙማን ይመዘገባሉ፡፡
የካንሰር ሕክምና ተደራሽነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ÷ በዚህም የተሟላ ሕክምናን የሚሰጡ የጤና ተቋማት ቁጥር 7 መድረሱን ተናግረዋል፡፡
በ32 ሆስፒታሎች ደግሞ ካንሰርን በመድኃኒት ብቻ የማከም የኬሞ ቴራፒ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡
ጥቁር አንበሳና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንዲሁም የጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ አይደር እና ሐረማያ የካንሰር ሕክምና ማዕከላት ኬሞና ራዲዮ ቴራፒን ጨምሮ ሌሎች የተሟሉ ሕክምናዎችን ይሰጣሉ፡፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ሰፊ የማስፋፊያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አማካሪው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል፡፡
በሌሎች የሕክምና ማዕከላት አገልግሎት የመስጠት አቅምን የሚያሳደጉ ሥራዎች በትኩረት እንደሚከናወኑም አመልክተዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.