Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ወደ ምግብ ዋስትና እና የግብርና ሽግግር በምናደርገው ጉዞ አንድ ሌላ እጥፋት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት ፈርመናል ነው ያሉት።

2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ይህ ሜጋ ፕሮጀክት በዓመት እስከ ሶስት ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ኢትዮጵያን ከዓለም ግንባር ቀደም አምራቾች አንዷ እንደሚያደርጋት ጠቁመዋል።

ፕሮጀክቱ በሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀው፤ ለዘመናት ለተፈተኑት አርሶ አደሮቻችን አስተማማኝ የማዳበሪያ አቅርቦት በማረጋገጥ ለምግብ ሉዓላዊነት መንገዳችንም ወሳኝ ርምጃ መውሰዳችንን ያመላክታል ብለዋል።

በመላው አኅጉሩ ኢትዮጵያ ያላትን ተወዳዳሪነት በማጠናከር ሕዝባችንን እና ነጋችንን የሚጠቅሙ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶችን የመከወን ጽኑ አቋማችንን ያሳያል ነው ያሉት።

የዛሬውን የፊርማ ስምምነት ተከትሎ ፋብሪካው በሚቆምበት ስፍራ ፕሮጀክቱን በይፋ የምናስጀምር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህን ታሪካዊ ጉዞ ጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል።

ለአርሶአደሮቻችን፣ ለኢኮኖሚያችን እና ለኢትዮጵያ ነገ ስንል እንጨርሰዋለን በማለት አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.