Fana: At a Speed of Life!

የቦትስዋና ምክትል ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቦትስዋና ምክትል ፕሬዚዳንት ንዳባ ኒኮዚናቲ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ም/ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በአዲስ አበባ ቆይታቸውም በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ፡፡
በተጨማሪም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አምባሳደር ብርሃኑ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.