ፑቲንና ኪምን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች የሚታደሙበት የቻይና ወታደራዊ ትርዒት…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች የሚሳተፉበት የቻይና ወታደራዊ ትርዒት በሚቀጥለው ሳምንት ይካሄዳል፡፡
“የድል ቀን” የተሰኘው የቻይና ወታደራዊ ትርዒት በዓል ቻይና ከጃፓን ጋር ያደረገችው ጦርነት እና የ2ኛው የዓለም ጦርነት 80ኛ ዓመት መታሰቢያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በፈረንጆቹ የፊታችን መስከረም 3 ቀን ለሚከበረው ወታደራዊ ትርዒትም አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በወታደራዊ ትርዒቱ የቻይና ጦር ሠራዊት አባላት እና ጡረታ የወጡ ወታደሮችን ጨምሮ ከ10 ሺህ በላይ ወታደሮች ይሳተፋሉ፡፡
በዚህ ደማቅና ተጠባቂ ትርዒት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡንን ጨምሮ የ26 ሀገራት መሪዎች እንደሚታደሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ በተለይም የፑቲንና ኪም መታደም ልዩ ድምቀት ከመስጠቱ ባለፈ ትልቅ አንድምታ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በበዓሉ መሳተፍ የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግን የዲፕሎማሲ ስኬት እንደሚያሳይ ነው የተገለጸው፡፡
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!