Fana: At a Speed of Life!

ድርጅቱ 13 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ጠቅላላ የዓረቦን ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 13 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ጠቅላላ የዓረቦን ገቢ ሰብስቧል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ታደሰ እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ፈጣን የኢኮኖሚ ለውጥ ላይ ትገኛለች።

ለዚሁ ለውጥም የመድን ኢንዱስትሪው የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው ያስገነዘቡት።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ2017 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን ጠቁመው÷ በበጀት ዓመቱ 13 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ጠቅላላ የዓረቦን ገቢ ሰብስቧል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥም 12 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ከጠቅላላ መድን ዘርፍ እንዲሁን 428 ሚሊየን ብር ከሕይወት መድን ዘርፍ እንደተገኘ አስረድተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለካሳ ክፍያ የወጣው ገንዘብ 6 ነጥብ 56 ቢሊየን ብር እንደደረሰ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት የካሳ ክፍያ ጋር ሲነጻር በ137 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.