Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎችን በመሰረታዊ ባህርተኝነት አሰልጥኖ አስመርቋል።

በባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጂስቲክስ አካዳሚ በተካሄደው የምረቃ መርሐ ግብር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዳሉት፤ ስልጠናው በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ ነው።

የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው በማለት ገልጸው፤ የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግድቡን ከጅማሮው አንስቶ ሲጠብቁ ቆይተዋል ብለዋል።

በለውጡ መንግስት አማካኝነት ግድቡን ከነበረበት ውድቀት በማዳን ለስኬት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል።

የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እና በአካዳሚው በኩል ባህርተኞችን ለዓለም ገበያ እያበቃ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በሁሉም መስክ እያንሰራራች ያለችውን ኢትዮጵያ ወደኋላ የሚመልሳት ኃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

የባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጂስቲክስ አካዳሚ ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ስልጠናው ዘመኑን የዋጀ ዓለም አቀፍ ይዘቱን የጠበቀ እንደሆነ ገልጸው፤ ሰልጣኞች አስፈላጊውን እውቀትና ባህሪ ታጥቀዋል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ለስልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ እውቅና መሰጠቱንም ኢዜአ ዘግቧል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.