Fana: At a Speed of Life!

የብር ሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ት/ቤት ወታደሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብር ሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ት/ቤት በ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መሰረታዊ ወታደሮች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

‎የመከላከያ ሠራዊት የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌ/ጄ ይመር መኮንን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ፣ የላቀ ወታደራዊ አቅም ያለው ጠንካራ ሠራዊት ተገንብቷል፡፡

ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ዕሳቤ ነፃ ሆኖ ሀገርንና ሕዝብን የሚያገለግል አስተማማኝ የመከላከያ ሃይል መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

የ42ኛ ዙር ተመራቂዎች በሥነ ልቦና፣ በአካል ብቃት፣ በቴክኔክና በስነ ምግባር በማነጽ ለዛሬው ምረቃ እንደበቁ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.