ተወዳዳሪና ዘመኑን የዋጀ ትውልድ ለመቅረጽ እየተሰራ ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተወዳዳሪ እና ዘመኑን የዋጀ እውቀት ያለው ትውልድ ለመቅረጽ በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፡፡
በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ማጠቃለያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በ2018 የትምህርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
በተለይም የመማሪያ መጽሐፍትን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ እንዲሰራጩ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢዎች መሆናቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ÷ ለዚህም ተወዳዳሪ፣ ብቁና ዘመኑን የዋጀ እውቀት እንዲሸምቱ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በክልሉ የተሰጠው ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት ሀገርን የሚገነቡ ተማሪዎችን ለመቅረጽ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡
ተማሪዎች በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ ማሳሰባቸውንም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት የዲጂታል ቴክኖሎጂና ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!