አህጉራዊ የንግድ ትስስርን በማጠናከር የአፍሪካን ኢኮኖሚ ማሳደግ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሳልማ ሐዳዲ በሀገራት መካከል ያለውን የእርስ በርስ የንግድ ትስስር በማጠናከር የአፍሪካን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይገባል አሉ።
4ኛው የአፍሪካ ንግድ ትርዒት ‘አፍሪካ የአዳዲስ ዕድሎች መግቢያ በር’ በሚል መሪ ሐሳብ በአልጄሪያ አልጀርስ እየተካሄደ ይገኛል።
ምክትል ሊቀመንበሯ በንግድ ትርዒቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላትን ሚና ለማሳደግ የእርስ በርስ የንግድ ትስስሯን ማጠናከር አለባት ብለዋል።
የንግድ ትስስሩ መጠናከር ከኢኮኖሚ በላይ በዓለም መድረክ ትርጉም ያለው የፖለቲካ ተሳትፎ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በአፍሪካ ውስጥ ያለው የንግድ ልውውጥ በ27 በመቶ ማደጉን አስታውሰው፤ ነገር ግን ከአህጉሪቱ አጠቃላይ የንግድ ልውውጥ 15 በመቶውን ብቻ እንደሆነ እና ባለፉት ስድስት ዓመታት በእርስ በርስ ንግድ ያሳየችው አበረታች እንቅስቃሴን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች የሚካሄዱ ተግባራት በሥራ ፈጠራ፣ እሴት በመጨመር፣ ኢንዱስትሪዎችን በማቋቋምና አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን በማውጣት የተመዘገበውን ስኬት አፍሪካውያንን ተጠቃሚ ለማድረግ ማዋል ይገባል ብለዋል።
የአፍሪካ መንግስታት እና ተቋማት የንግድ መሰናክሎችን በማስወገድ፣ መሠረተ ልማትን በማጠናከር፣ ምቹ ፖሊሲ እና የፋይናንስ ስርዓቶችን በመዘርጋት የአህጉሪቱን ሁለንተናዊ አቅም እንዲያሳድጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በንግድ ትርዒቱ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ75 ሀገራት የተውጣጡ 2 ሺህ የንግድ ተቋማት እየተሳተፉ እንደሆነ የአፍሪካ ህብረት መረጃ አመልክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!