የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ በምክክር ችግሮችን በመፍታት ልብ ለልብ ተገናኝቶ መጓዝ ይገባል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥ በምክክር ችግሮችን በመፍታት እጅ ለእጅ ተያይዞና ልብ ለልብ ተገናኝቶ መጓዝ ይገባል አለ።
ምክክር ኮሚሽኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተወካዮች የተሳተፉበት የቅድመ ምክክር መድረክ በትግራይ ክልል መቐለ አካሂዷል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም በመድረኩ እንዳሉት፤ በሀገራዊ ምክክሩ የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በምክክር ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ያስፈልጋል።
በዚህም መሰረት በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው የቅድመ ምክክር መድረክ ለዚህ ስኬት ጥሩ መሰረት የሚያኖር ነው ብለዋል።
ለችግሮች ሁሉ ቁልፉ መፍትሄ ምክክር በመሆኑ እድሉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ማስገንዘባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
የመድረኩ ተሳተፊዎች ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር በዘላቂነት ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆናቸው ማረጋገጣቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት ለመጀመርና ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ቀደም ሲል ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውይይት መደረጉን መግለፃቸው ይታወሳል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!