Fana: At a Speed of Life!

በነጻ የንግድ ቀጣና ስርዓት መሻሻል እያሳየ ያለው አህጉራዊ የንግድ ልውውጥ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስርዓት አህጉራዊ የእርስ በርስ የንግድ ልውውጥ እያደገ እንዲመጣ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው አለ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተቋም።

የአፍሪካ ህብረት፣ አፍሪኤግዚም ባንክ እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ተቋም በመተባበር ያዘጋጁት 4ኛው የአፍሪካ ንግድ ትርዒት ‘አፍሪካ የአዳዲስ ዕድሎች መግቢያ በር’ በሚል መሪ ሐሳብ በአልጄሪያ አልጀርስ እየተካሄደ ይገኛል።

የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ተቋም ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ እንዳሉት፤ አፍሪካ ያላትን ሀብት በመጠቀም ዕድገቷን ሀገራት እና ተቋማት በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል።

አህጉራዊ ትብብርን ለማሳደግ የእርስ በርስ ንግድ ትስስርን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እየተመዘገበ ነው ማለታቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ አመልክቷል።

በተለይም ምርቶችንና አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ስምምነቶች በመድረስ፣ የገበያ ትሰስርን በመፍጠር ረገድ መሪዎች ቁርጠኝነት ማሳየት ጀምረዋል ነው ያሉት።

በአህጉሪቱ የሚካሄደው የእርስ በርስ ንግድ ልውውጥ የሀገራትን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የግሉ ዘርፍ በተለይም ኩባንያዎችን ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ውጤታማ መሆን እንደተቻለ ተናግረዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከታሪፍ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ዝንባሌዎችና አዝማማሚያዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የእርስ በርስ ንግድ ልውውጥን ማሳደግ ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የአፍሪካ ነጸ ንግድ ቀጣና ስርዓትን የሚፈትኑ ጉዳዮች እንዳሉ አንስተው፤ የጉምሩክ አሰራሮችን ቀልጣፋ ማድረግ እና የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.