እኛ አፍሪካውያን ለችግሮቻችን መፍትሔ ማምጣት እንችላለን
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ የምግብ ሉአላዊነት ህብረት እኛ አፍሪካውያን ለራሳችን ችግሮች እንደ አፍሪካውያን መፍትሔ ማምጣት እንችላለን አለ።
የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ህብረት እና የአግሮ ኢኮሎጂ ፈንድ በጋራ ያዘጋጁት የወጣቶች የአግሮ ኢኮሎጂ ዘርፍ ውድድር ተካሂዶ ለአሸናፊዎች ሽልማት ተበርክቷል።
የአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ህብረት ዋና አስተባባሪ ሚሊዮን በላይ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ውድድሩ አፍሪካ የጀመረችውን የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ጉዞ ያጠናክራል።
የምግብ እጥረት፣ የተቀነባበሩ ምግቦች እንደካንሰር ላሉ ገዳይ በሽታዎች አጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸው እና የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ አሁን ላይ በዓለም ዙሪያ ያሉ ችግሮች ናቸው ብለዋል።
በተጨማሪም በባህል መሸርሸር ሳቢያ የሀገር በቀል ምግቦች ከማዕድ መራቃቸው፣ ሀገር በቀል የግብርና ዕውቀቶች እንዳይዳብሩ በቂ ስራ አለመሠራቱ፣ የአህጉሪቱ የዘርፉ ፖሊሲዎች ለውጭ አካላት ጥቅም ተስማሚ ብቻ ሆነው እንዲቀረፁ ከውጭ አካላት የሚደረግ ተፅዕኖ የችግሩ አካል መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ህብረቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የምግብ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ስራዎች ግባቸውን እንዲመቱ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠው፤ እኛ አፍሪካውያን ለችግሮቻችን መፍትሔ ማምጣት እንችላለን ብለዋል።
በግብርና ዘርፍ ወጣቶችን ማሳተፍ እና የፈጠራ ስራዎቻቸውን ማበረታታት ከመፍትሔዎቹ ውስጥ አንዱ በመሆኑ በትኩረት እየተሰራበት መሆኑን አመልክተዋል።
በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የኢኖቬሽንና ስራ ፈጠራ ልማት ዴስክ ኃላፊ ብርሀኑ አደሬ በበኩላቸው፤ ውድድሩ ወጣቶች ሀገር በቀል መፍትሔዎችን በማበልፀግ በሀገራቸው ኢኮኖሚ ላይ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ይረዳቸዋል ነው ያሉት።
ከውጭ የምናስገባውን ምርት በመቀነስ የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት ለወጣቶች እንዲህ አይነት ዕድሎች መኖራቸው እጅግ በጣም ጥሩ አማራጭ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ስርዓት እና የአግሮኢኮሎጂ ጥምረት ዋና ዳይሬክር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር)፤ ይህ ጅምር ወጣቶችን ስለሚነያቃቃ ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር ጥምረቱ በቅርበት ይሰራል ነው ያሉት።
በዘርፉ ያለውን መረጃ ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል አግሮኢኮሎጂ ቤተመፃህፍት ለማበልፀግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሳፍንት ብርሌ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!