የሀገር ዕድገትና ብልፅግና ከግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውጪ አይታሰብም – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ የሀገር ዕድገት እና ብልፅግና ከግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውጪ የሚታሰብ አይደለም አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ ለማፅናት በጀመርነው ተግባራዊ ሥራ ሀገራዊ ተቋማት ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።
ዛሬ በጽናት ቀን በሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ የተዘጋጀውን አውደ ርዕይ መመልከታቸውን ገልጸው፤ በደም እና በአጥንት የጸናች ሀገርን በኢኮኖሚ ልዕልናዋ እንዲረጋገጥ የግሉ ዘርፍ በልማቱ የሚያበርክተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ድርሻ ይይዛል ነው ያሉት።
ለኢትዮጵያ በተለያዩ ፈታኝ ወቅቶች ጭምር በጽናት በመስራት ሕዝባዊነታቸውን ካረጋገጡና ለሀገር ኢኮኖሚ እንዲሁም ማኅበራዊ ጉዳዮቻችን ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ ተቋማት ውስጥ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አንዱ መሆኑን አስታውሰዋል።
ተቋሙ ባሉት 45 ኩባንያዎች ለሀገር እና ሕዝብ ቀጥተኛ ድጋፍ እያበረከተ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከዚህም ባለፈ ምርቶቹን በቅናሽ ዋጋ ለኅብረተሰቡ ማቅረቡ፣ ሌሎች ተቋማት የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው በር መክፈቱና የካበተ ልምዱን ለማሳወቅ ይህንን አውደ ርዕይ ማዘጋጀቱ በአርአያነት የሚቀርብ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ የሀገር ዕድገት እና ብልፅግና ከግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውጪ የሚታሰብ አይደለም ነው ያሉት።
ለዚህ ደግሞ እንደ ሚድሮክ ሁሉ ዓመታትን የተሻገር ልምድ ያላቸው ተቋማት ልምዶቻቸውን ማጋራት እና ህዝባዊነታቸውን በማረጋገጥ ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት ላይ ለማፅናት ያላቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!